Lidia Anteneh (ሊዲያ አንተነህ)
Lyrics for Singer Lidia Anteneh's single songs
የሊዲያ አንተነህ የነጠላ መዝሙሮች
ለእኔ ነው
እንዴት ያለውን ፍቅርህን ነው ያደልኸኝ
የማይነጥፈውን ሰላምህን ያካፈልኸኝ
እንዴት ያለውን ምሕረት ነው ያገነንከው
ለጠፋሁትኝ መስዋዕት ሆነህ የቀረብከው
እንዴት ያለውን ክብር ነው ያለበስከኝ
በጸጋህ ብዛት ድነትን ያጎናጸፍከኝ
እንዴት ያለውን ውስጣዊ ሰላም ደስታ
አበዛህልኝ ጋረድከኝ ‘ካለም ሁካታ
ያባትህን ፈቃድ ልትፈጽመው ፍጹም ታዘህ
አቀረብከኝ ዳግም ወደ ራስህ ቤዛ ሆነህ
አንተ የእኔ አባት እኔም የአንተ ልጅህ ሆኛለው
ማንም ላይለየን ኪዳናችን በቅዱስ ደምህ ነው
ጽድቅ አልብሰኸኝ ኩነኔን ከኔ አርቀኸዋል
‘ሚከሰኝ የለም አንዴ ወደህ መርጠኸኛል
ትማልዳለህ ልታኖረኝ በጽድቅ ህይወት
ዘመኔን ከብረህ ዘላለሜን በውበት ልታትታይበት
ለእኔ ለእኔ ነው ይሄንን ሁሉ የሆንከው
ለእኔ ብለህ ነው ደም ግባትህን ውበት ያጣኸው
አዎ ለእኔ ነው ክብርህን ትተህ የተዋረድከው
በሚጠሉህ ፊት ጎልጎታ ላይ የታየኸው
ኢየሱስን በማወቅ ወደሚገኘው በረከት
እንዲሁ ገባሁ ጽድቅ ሆነህልኝ በዕምነት
ስራህ ክብሬ ሆኖ ተሾኩኝ እንደ መልካም ልጅ
በክብር ስምህ ተጠራሁ ተያዝኩኝ በአንተ እጅ
በምን ወደድከኝ ስል ለራሴም ይገርመኛል
ከእኔ አንዳች የለም አውቃለሁ ይሄ ገብቶኛል
እንደምትወደኝ ለሞት ታዘህ አሳይተኻል
አቤት እላለሁ ከአእምሮዬ በላይ ሁሉ ሆኖብኛል
ለእኔ ለእኔ ነው ይሄንን ሁሉ የሆንከው
ለእኔ ብለህ ነው ደም ግባትን ውበት ያጣኸው
አዎ ለእኔ ነው ክብርህን ትተህ የተዋረድከው
በሚጠሉህ ፊት ጎልጎታ ላይ የታየኸው
በፊትህ ላፍስሠው
የሚያረካህ ነገር አንተ ምትፈልገው
ይገኝ ይሆን ብዬ ይዤ መጥቻለው
አንደበቴን ሙላው በብዙ ምስጋና
ዝማሬ እና ቅኔ ትወዳለህና
በቀን ስመላለስ ማዳንህ በትሬ
በለሊት ሆነልኝ በአፌ ላይ ዝማሬ
እንደ ንጋት ብርሃን በላዬ አብርተህ
መሰማሪያ አገኘው እረኛዬ ሆነህ
ሚገባህን ሁሉ በፊትህ ላፍስሠው
ምንም ነገር የለም ‘ላንተ የማልሠዋው
ያየሁት ምህረትህ ከቃላቴ በልጧል
መላው አካላቴ ክብር ይሠጥሃል
በማዳን ብርቱ ነህ እኔን አግኝተሃል
ጠላትህ ሳለሁኝ ወደህ ቀርበኸኛል
ቀኝህ ሲያስመልጠኝ ከጠላቴ ዛቻ
እጅህ ስለያዘኝ ሆንኩኝ ያንተ ብቻ
‘ሚገባህን ሁሉ በፊትህ ላፍስሠው
ምንም ነገር የለም ‘ላንተ የማልሠዋው
ያየሁት ምህረትህ ከቃላቴ በልጧል
መላው እኔነቴ ክብር ይሠጥሃል
‘ሚገባህን ሁሉ በፊትህ ላፍስሠው
ምንም ነገር የለም ‘ላንተ የማልሠዋው
ያየሁት ምህረትህ ከቃላቴ በልጧል
መላው አካላቴ ክብር ይሠጥሃል
ድንቅ ነህ አምላኬ ድንቅ ነህ
ግሩም ነህ ኢየሱሴ ግሩም ነህ
አባት ነህ ጌታዬ አባት ነህ
መልካም ነህ ኢየሱሴ መልካም ነህ
አመልክሀለሁ እየኖርኩ
አንተን እያመለኩ አንተን እያከበርኩ
ውዴ እያመለኩ ውዴ እየወደድኩ
ላንተ እየዘመርኩ አመልክሀለሁ እየኖርኩ
አንተን እየወደድኩ አመልክሀለሁ እየኖርኩ
በደስታ በሙሉ ልቤ
ሳልሸራርፍ ይኸው ቃላቴ
ባይገኝ ሚመጥንህም አመልክሀለሁ እየኖርኩ
ትላንትን በሕያውነትህ
ዛሬንም በዐዲስነትህ
ነገንም በዘላለም ቤትህ
ላምልክህ ኾኜ በፊትህ
ኑሮዬ ይኹን መሥዋዕትህ
ሕይወቴም ይኸው በፊትህ
በፍቅር፣ በእምነት በተስፋ አመልክሀለሁ እየኖርኩ
ትላንትን በሕያውነትህ
ዛሬንም በዐዲስነትህ
ነገንም በዘላለም ቤትህ
ላምልክህ ኾኜ በፊትህ
አመልክሀለሁ እየኖርኩ