Binyam Yonas (ቢንያም ዮናስ)
Lyrics for Singer Binyam Yonas's single songs
የቢንያም ዮናስ የነጠላ መዝሙሮች
Yisema Bealem ይሰማ በዓለም
ይሰማ በዓለም እምነቴ ኢየሱስ ነው
ሰንደቅ ዓላማዬ ከፍ ከፍ የማደርገው
ከቶ ማላፍርበት ክብሬ እርሱ ነውና
ዕወቁት እላለሁ የጌታዬን ዝና
ዕወቁት እላለሁ የኢየሱሴን ዝና
ዕወቁት እላለሁ የጌታዬን ዝና
ያመነበት ፍጹም ከውጪ አይጣልም
ከከበረው እጁ ማንም አይነጥቀውም
አጥብቆ ይይዛል በኃያሉ ፍቅሩ
የምህረት አምላክ ነው እና ርህሩህ
ወደ አብ የሚያደርስ መንገድ እና እውነት
ትንሣኤ የሆነ ከሞት ወዲያ ህይወት
ከሰማይ የመጣ የህይወት መና ነው
ፍሬን የሚሰጠን የወይኑ ግንድ ነው
ከአስፈሪው ጨለማ ጌታ ይታደጋል
ሽክምና እስራት በስሙ ይፈታል
ነጻ የሚያውጣ አንድ ነው እውነቱ
አርነት የሚሰጥ በማዳኑ ብርቱ
በማዳኑ ብርቱ * 2
አርነት የሚሰጥ
በማዳኑ ብርቱ
Kalihen wededkut – ቃልህን ወደድኩት
ቃልህን ወደድኩት ከሁሉ አስበልጬ
ወደ እቅፍህ መጣሁ አንተኑ መርጬ
ከብዙሃን ጥበብ ረቂቅ ንግግር
ነፍሴ እጅግ ወደደች መሆን ከእግሮችህ ስር
በሰው ብልሀት ተረት ከቶ ያልተፈጠረ
የዘላለም እውነት ከጥንት የነበረ
በልቤ ላይ በርቶ የቃልህ ብርሀን
ፈቃድህ ተገልጦ ሆኖልኛል መዳን
ስምህ በከንፈሬ እንደ ጅረት ሲፈስ
በመንፈስ ቅዱስህ ውስጠቴ ሲታደስ
በልቦናዬ ውስጥ እውነትህ ሲሞላ
ለአንድያ ነፍሴ እረፍት ሆነ ተድላ
እኔን አሰማርተህ በለምለም መስክህ ላይ
ጥሜን እያረካ ወደሌላ እንዳላይ
ጥላ ሆነህኛል የህይወት ፍካሬ
ህያው አርገህኛል የአንደበትህ ፍሬ
አንተን የሚሰማ ፈቃድህን የሚወድ
በክፉዎች ምክር ልቡ የማይጠመድ
በዋዘኞው ወንበር መቀመጥ የጠላ
ራሱን የማያስገኝ ለጊዜያዊ ተድላ
በህግህ ሁልጊዜ እጅግ ደስ እያለው
በቀን እና በሌት ቃልህን እያሰበው
ብዙ ፍሬ ማፍራት በእርሱ ዘንድ አለ
በህይወት ምንጭ ዳር ስለተተከለ
Yenafekegn | የናፈቀኝ
የናፈቀኝ ያንተ መንፈስ ነው
የናፈቀኝ መገኘትህ ነው
አላስችልህም አለኝ የውስጤ ረሀቡ
መንፈስህ በእኔ ይፍሰስ በመቅደሱ
አይገለፅም አይብራራም ሀልዎት የእኔጌታ
ማጣጣም ነው የምችለው በመንፈስህ እሞላለሁ
ጥግ አልይዝም ልትሰራ ወደህ በልጆችህ መሀል ስትንቀሳቀስ
እጄን ያዘኝ እልሀለው ግርማን በእኔ ላይ እስከማየው
ምታረካ አፅናኝ የህይወት ውሀ አረስርሰኝ በህልውናህ እሳት
ልዳስስ ልሰማህ እወዳለሁ ክብርህን ማየት ለእኔ ደስታ ነዉ
ከአድማስ ማዶ እንደማያት ፀሀይ ሩቅ አይደለህም ምትጠልቅብኝ ብርሀን
እዚሁ ነህ በውስጥ ሰውነቴ ወርሰክ ልየው መላውን እኔነቴ