Fenan Befekadu (ፈናን በፍቃዱ)
Lyrics for Singer Fenan Befekadu's single songs
የፈናን በፍቃዱ የነጠላ መዝሙሮች ግጥም
ውሰደዉ | Wusedew
ዘላለማዊ አልፋ ኦሜጋ ለሆንከው
የምስጋናንም ዘውድ በራስህ ለጫንከው
ያንን ፊትህን ብሩህ ግርማህን እያየሁ
ዘውትር ዙፋንህ ስር እሰግዳልሁ
ውሰደው መስዋእቴን ውሰደው/ X2
አምልኮዬ ላንተ ነው የሚገባው/
ክብርን ሁሉ ይዤልህ መጥቻለው
የታረድከው በግ አንተ
ህዝቦችን ከነገድ ዋጅተህ
ካህናት አድርገሃል
ንግስና ይገባሃል
ውሰደው መስዋእቴን ውሰደው/ X2
አምልኮዬ ላንተ ነው የሚገባው/
ክብርን ሁሉ ይዤልህ መጥቻለው
መፅሃፉን ወስደህ
ማህተሙንም ልትፈታ
ይገባሃል አንተ የታረድከው ጌታ
የይሁዳ ነገድ የሆንከው
አንተ ኢየሱስ ድል ነስተሃልና
ዘላለም ልትነግስ
ሃይልና ባለጠግነት
ጥበብንና ብርታት
ክብርን ሁሉ ተላብሰሃል
አምልኮ ይገባሃል
ውሰደው መስዋእቴን ውሰደው/ X2
አምልኮዬ ላንተ ነው የሚገባው/
ክብርን ሁሉ ይዤልህ መጥቻለ
ዘላለማዊ አልፋ ኦሜጋ ለሆንከው
የምስጋናንም ዘውድ በራስህ ለጫንከው
ያንን ፊትህን ብሩህ ግርማህን እያየሁ
ዘውትር ዙፋንህ ስር እሰግዳልሁ
ውሰደው መስዋእቴን ውሰደው/ X2
አምልኮዬ ላንተ ነው የሚገባው/
ክብርን ሁሉ ይዤልህ መጥቻለው
የታረድከው በግ አንተ
ህዝቦችን ከነገድ ዋጅተህ
ካህናት አድርገሃል
ንግስና ይገባሃል
ውሰደው መስዋእቴን ውሰደው/ X2
አምልኮዬ ላንተ ነው የሚገባው/
ክብርን ሁሉ ይዤልህ መጥቻለው
መፅሃፉን ወስደህ
ማህተሙንም ልትፈታ
ይገባሃል አንተ የታረድከው ጌታ
የይሁዳ ነገድ የሆንከው
አንተ ኢየሱስ ድል ነስተሃልና
ዘላለም ልትነግስ
ሃይልና ባለጠግነት
ጥበብንና ብርታት
ክብርን ሁሉ ተላብሰሃል
አምልኮ ይገባሃል
ውሰደው መስዋእቴን ውሰደው / X2
አምልኮዬ ላንተ ነው የሚገባው/
ክብርን ሁሉ ይዤልህ መጥቻለው
ሃሌሉያ/4 ለታረደው በግ ይገባዋል
ለታረደው በግ ለኢየሱስ
አምላካችን ዘላለም ይንገስ
ሀይልም ሞገስ ባለጠግነት
ምስጋናም ክብር
ጥበብም ብርታት
ኢየሱስ
የህይወት የህይወት መልህቅ
በፍቅርህ የያዝከኝ እንዳልርቅ
የህይወት የህይወት መልህቅ
በፍቅርህ የያዝከኝ እንዳልርቅ
ኢየሱስ አንተ ብቻ ነህ
ኢየሱስ ኢየሱስ
ማን እንደ አንተ ማን እንደ አንተ ይሆናል ይሆናል
ኢየሱስ ኢየሱስ
ማን እንደ አንተ ማን እንደ አንተ ይሆናል ይሆናል
ክብሬ ነህ ክብሬ ነህ
ማን እንደ አንተ ማን እንደ አንተ ይሆናል ይሆናል
ትለይብኛለህ ትለይብኛለህ
ማን እንደ አንተ ማን እንደ አንተ ይሆናል ይሆናል
አንተን ቢያይ እንጂ በዚች ከንቱ አለም
መኖር ሚመኝ የለም
ግን መኖሬን ወደድኩት ይበልጥ አንተን ሳውቅህ
ስለገባኝ ፍቅርህ
ለእኔ ህይወት አንተ ሞት እንዲሆን ጥቅሜ
ለአንተ ነው መኖሬ
ቢሆንም አውቃለው ለእኔ የሚሻለው
እላይ ከአንተ ጋር ነዉ
ለአንተ ካለኝ ፍቅር የሚለየኝ ነገር
ከቶ አይኖርም ከቶ አይኖርም ለዘለዓለም በፍጹም
ከአንተ ውጪ ህይወት እንደሌለ ገብቶኛል
ማን እንደ አንተ ማን እንደ አንተ ይሆናል ይሆናል
አንተን ቢያይ እንጂ በዚች ከንቱ አለም
መኖር ሚመኝ የለም
ግን መኖሬን ወደድኩት ይበልጥ አንተን ሳውቅህ
ስለገባኝ ፍቅርህ
ለእኔ ህይወት ክርስቶስ ሞት እንዲሆን ጥቅሜ
ለአንተ ነው መኖሬ
ግን ይሄንን አውቃለሁ እጅግ የሚሻለው
እዛው እያየውህ ነው
ኢየሱስ ኢየሱስ
ማን እንደ አንተ ማን እንደ አንተ ይሆናል ይሆናል
መንፈስ ቅዱስ | Menfes Kidus
በእንግድነት አለም ስኖር
የማይለየኝ መፅናኛዬ
ከአብ ዘንድ ተሰቶኛል
እንዲሆነኝ መያዣዬ
በእንግድነት አለም ስኖር
የማይለየኝ መፅናኛዬ
የልብ የውስጤን ሚረዳ
የማይተወኝ ቤተኛዬ
ብቻዬን አይደለሁም
አለኝ የሚያፅናናኝ
ብቻዬን አይደለሁም
አለኝ የሚመራኝ
ብቻዬን አይደለሁም
አለኝ መንፈስ ቅዱስ
ብቻዬን አይደለሁም
አለኝ ቅዱስ መንፈስ
የፍቅር መንፈስ የደስታ የሚመራኝ ሚያስተምረኝ
የሰላም መንፈስ የዕምነት የሚያፀና ሚኖር አብሮኝ
የፍቅር መንፈስ የደስታ የሚመራኝ ሚያስተምረኝ
የሰላም መንፈስ የዕምነት የሚያፀና ሚኖር አብሮኝ
ብቻዬን አይደለሁም
አለኝ የሚያፅናናኝ
ብቻዬን አይደለሁም
አለኝ የሚመራኝ
ብቻዬን አይደለሁም
አለኝ መንፈስ ቅዱስ
ብቻዬን አይደለሁም
አለኝ ቅዱስ መንፈስ
(ብቻዬን አይደለሁም) X12
መድኃኒቴ | Medhanite
ገና በማለዳ ብርሃን ሳይፈነጥቅ
ጨረቃም ቦይታዋን ለፀሃይ ሳትለቅ
አይኖቼ ተከፍተው ከእንቅልፌ ስነቃ
እየሱስን እሻለው
እየሱስን ጠራለው ሌሊቱ ሲነጋ
ሲነጋ ሲነጋ እየሱስን ልጠጋ*2
ሲነጋ ሲነጋ ወደ እየሱሴ ጋ
በቀትር ምሳ ሰዓት ድካም ሲመጣብኝ
ልቤ እረፍት ሲሻ ዝለት ሲጫጫነኝ
ከቶ ማልዘነጋው የነፍሴ ረሃቧ
እየሱስን እሻለው
እየሱስን ጠራለው
ጥጋቤ ነውና !
በቀትር በቀትር እየሱስ ላናግር
በቀትር ከእሱ ጋር ልማከር X2
በቀትር
ማታ አመሻሽ ላይ አይኔ ባይከደን
ፀሃይም ስትሸሽ ድካም ሲሰለጥን
ሰውነት ሲያቅተው መቋቋም እንቅልፍን
መተኛት አልሻም ቀኑም አይዘጋም
ሳልጠራው ስምህን!
በምሽት በምሽት እየሱስን ልጥራበት
በምሽት ከሱጋ ልጫወት በምሽት
በምሽት ለነፍሴ ላስታዉሳት በምሽት
መድሃኒቴ ስምህ ጠራለው X2
ጌታ እየሱስ ስምህን ጠራለሁ
ቀርበህ ሳለህ ስምህ ጠራለው
የኔ አፀናኝ ስምህ ጠራለው
መድሃኒቴ ስምካ ክፅውህዬ X2
ጎይታ እየሱስ ስምካ ክፅውህዬ
ፈይሳኮ መቃኬን ዋማ
ጎፍታ እየሱስ መቃኬን ዋማ
ጋር ጋራ ኮ መቃኬን ዋማ
መድሃኒቴ ስምህን ጠራለው
የኔ አፀናኝ ስምህን ጠራለው
መዳኛዬ ስምህን ጠራለው!
መልካም ነህ
የማለዋውጠው እውነት ነው
በሁኔታዎች የማላጥፈው
የሚመሰክረው ህይወቴ
መልካምነትህን ነው አባቴ
የሚዘምረው አንደበቴ
መልካምነትህን ነው አባቴ
ኢየሱስ መልካም ልበልህ /መልካም ነህ/
እንዲህ ነው እኔ የማውቅህ /መልካም ነህ/
መመስከር ነው የኔ ስራ /መልካም ነህ/
መንገድን እንደምትመራ /መልካም ነህ/
መልካም ነህ (*4)
ከራስህ ከማንነትህ /መልካም ነህ/
በጎ ነው ሁሌም አላማህ /መልካም ነህ/
ፈተናዬን ታግዛለህ /መልካም ነህ/
በዛም ውስጥ ድል ትሰጣለህ /መልካም ነህ/
(መልካም ነህ) X4
ላይገባኝ ይችላል እጅግ ብዙ ነገር
እንዲህ እንዲያ ብዬ በእርግጥ ለመናገር
ግን አንዱ ሁልጊዜም ለማለት ምደፍረው
ማልሸሸው እውነትህ መልካምነትህ ነው
(ማልክደው እውነትህ መልካምነትህ ነው)
(ማወራው እውነትህ መልካምነትህ ነው)
(መልካም ነህ) X4