Meron Alemu (ሜሮን አለሙ)
Lyrics for Singer Meron Alemu's single songs
የሜሮን አለሙ የነጠላ መዝሙሮች
ኢየሱስ
ከሁሉ ደምቀህ ታየህ ሞገስህ ሁሉን ሸፈነ
ከስሞች ሁሉ በላይ ከፍ ያለ ስም ተሰጠህ
እየሱስ እየሱስ
እየሱስ ስልጣን አለው ስምህ
እየሱስ ከ ስሞች ሁሉ በላይ
እየሱስ የጠራህ ሁሉ ዳነ
እየሱስ
እየሱስ ሀይል አለው ስምህ
እየሱስ ከ ስሞች ሁሉ በላይ
እየሱስ ያመነህ ሁሉ ዳነ
እየሱስ
አንተን በልቡ ላመነ ማዳንህን ለመሰከረ
መንገድ ሆነኸዋል አብጋር ሚደርስበት
እውነተኛ መዳን የዘላለም ህይወት
መንገድ ሆነኸዋል አብጋር ሚደርስበት
እውነተኛ መዳን የዘላለም ህይወት
ሀሌሉያ(8*)
እንደሚፈስ ዘይት ስምህ መድመቂያና ውበት
ያለልክ ከፍ ብሎ ገዛ ሁሉንም ጠቅልሎ
እየሱስ እየሱስ
እየሱስ ስልጣን አለው ስምህ
እየሱስ ከ ስሞች ሁሉ በላይ
እየሱስ የጠራህ ሁሉ ዳነ
እየሱስ
እየሱስ ሀይል አለው ስምህ
እየሱስ ከ ስሞች ሁሉ በላይ
እየሱስ ሁሉ ያመነህ ዳነ
እየሱስ
ደስ እያለኝ በፍቅርህ ተይዤ
ደስ እያለኝ በውበትህ ተማርኬ(2*)
ነፍሴ ትፈስልሀለች በፍቅርህ ተይዛለች
በውበትህ ተሸንፋ በምስጋና ተሞልታለች
ሀሌሉያ*8
በብርሃንህ
የከበበኝ ጨለማ ተስፋ የማጣት ደመና
እየጋረደው ትኩረቴን ብዥ ያደረገው መንገዴን
አንተን ሳስብ ይገፈፋል ጽልመቴ ወገግታ ይሆናል
ሳይህ ተስፋን እሞላለሁ በብርሃን እጓዛለሁ
ጨለማዬን አሸንፈሃል በብርሃንህ ብርሃን አየሁ(2*)
በብርሃን ብርሃን አየሁ (4*)
አንተን ማወቅ ብርሃኔ ፊትህ እርካታ ደስታዬ
ወዳን’ተ እጠጋለሁ ፊትህን እሻለሁ
እፈልግሀለው (2*)
ሳይህ ተስፋን እሞላለሁ በብርሃን እጓዛለሁ
ጨለማዬን አሸንፈሃል በብርሃንህ ብርሃን አየሁ(2*)
በብርሃን ብርሃን አየሁ (4*)
ውዴ ሳስብህ ልቤ ይበረታል
የቃልህ እውነት ተስፋን ይሰጠኛል
ዛሬም ነገም እታመንሀለው
በብርሃንህ ውስጥ ብርሃንን እያየሁ
አንተን ማወቅ ብርሃኔ ፊትህ እርካታ ደስታዬ
ወዳን’ተ እጠጋለሁ ፊትህን እሻለሁ
እፈልግሀለው (2*)
አንተን ማወቅ ብርሃኔ ፊትህ እርካታ ደስታዬ
ወዳን’ተ እጠጋለሁ ኢየሱስ እላለሁ
እፈልግሀለው(2*)
ሳይህ ተስፋን እሞላለሁ በብርሃን እጓዛለሁ
ጨለማዬን አሸንፈሃል በብርሃንህ ብርሃን አየሁ(2*)
በብርሃን ብርሃን አየሁ