Yohanes Sisay (ዮሐንስ ሲሳይ)
Lyrics for Singer Yohanes Sisay's single songs
የዮሐንስ ሲሳይ የነጠላ መዝሙሮች
የነፍሴ እርካታ
የነፍሴ እርካታ ፍፁም ደስታዬ
የምሰወርብህ ጥላ ከለላዬ
የመኖሬ ትርጉም የህይወቴ ፍስሃ
ኢየሱስ አንተው ነሀ
አጥብቄ የምሻህ ጠዋትና ማታ
ነፍሴ የምትወድህ ብቸኛ ሙላቷ
ዛሬም ትሻሀለች ከሁሉ አብልጣ
ወደሷ እስክትመጣ
አንተን አንተን ትልሀለች x4
ድጋፌ ምርኩዜ የህይወቴ ዋና
አንተን መፈለጌ መች በእኔ ሆነና
አቅሜ ብርታቴ ፍለጋዬ አንተው ነህ
ዘላለም ምመካብህ
ፈልጌ ማልጠግበው ብቸኛ ጉጉቴ
ሳገኝ ሚብስብኝ የነፍስ ጥማቴ
አሁንም አሁንም ይራባል ውስጠቴ
መንፈስህን በህይወቴ
አንተን አንተን ይልብኛል x4
ፊትህን ሳየው ሳገኝህ በህልውናህ
ትረካለች ነፍሴ ከጥልቅ ጥሟ
ካንተጋ ያለኝ ህብረት ነው የኔ ፍስሃ
ካንተጋ ያለኝ ሰላም ነው የኔ ደስታ
ካንተጋ ስሆን ይለያል የኔ ፍስሃ
ካንተጋ ስሆን ይለያል የኔ እርካታ x2
ኢየሱስን እዘምራለሁ
የዘላለም ደስታዬ ነህ
የዘላለም እረፍቴ ነህ
ባንተ ደስታ ሆነልኝ መልካም ነህ
ባንተ እረፍት ሆነልኝ መልካም ነህ
ባንተ ሰላም ሆነልኝ መልካም ነህ
እንዴት እረሳለሁ ያለፈውን ሁሉ
አስታውሰዋለሁ በረሀ ሀሩሩን
ከየት እንዳነሳኸኝ መቼም አረሳውም
ታሪኬ ብዙ ነው ብናገር አያልቅም
ዛሬ ደግሞ አልፎ በመልካምነትህ
ይኸው ዘምራለው አምሮብኝ በቤትህ
እድሉን ካገኘው ፀጋህ ከበዛልኝ
ገና እዘምራለሁ ጌታ ክበርልኝ
ገና እዘምራለሁ ጌታ ክበርልኝ
(የኔ መልካም መልካም ነህ መልካም ነህ
የኔ መልካም መልካም ነህ መልካም ብቻ) X2
መች ይመስል ነበር እንደዚህ የሚሆን
ክንድህ ባትረዳኝ ከእኔ ጋር ባትሆን
እኔ ያላመሰገንኩ ማን ሊዘምርልህ
ኢየሱስን እላለሁ በቀረኝ ዘመን
ኢየሱስን እዘምራለሁ
መልካምነትህን ለአለም አወራለሁ
መድኃኒቴ እወድሃለሁ
መልካምነትህን በአይኔ አይቻለሁ/X2
(የኔ መልካም መልካም ነህ መልካም ነህ
የኔ መልካም መልካም ነህ መልካም ብቻ)X2
አየዋለው
መዳን የቻልኩበት የኢየሱሴ ህይወት
እንባዬን ከአይኔ አብሶ በሳቅ የቀየረበት
ከዘላለም እሳት ህይወቴን የታደጋት
እሱ ነው መድሃኒቴ ዛሬም ልዘምርለት
ላየው ምናፍቀው የዘላለም ተስፋዬ
ልቤን እርፍ ያለበት የነፍስ መታመኛዬ
በክብር ታጅበህ እስከምትመጣ
እጠብቅሃለው ኢየሱስ የኔ አሌኝታ
አየዋለው መድሃኔቴ
የአይኔ እረፍት ነህ ኢየሱሴ
አየዋለው መድሃኔቴ
የአይኔ እረፍት ነህ ኢየሱሴ
አየዋለው መድሃኔቴ
የአይኔ እረፍት ነህ ኢየሱሴ
አየዋለው መድሃኔቴ
የአይኔ እረፍት ነህ ኢየሱሴ
ከዚች አለም ስቃይ ምገላገልበት
ከደመናት ጋር ሆነህ ኃይል ሁሉ አንተን ሚያይበት
ያለህ የነበርከው ደግሞ ምትመጣበት
ደስታዬ ፍፁም ሆኖ ክብርህን የማይበት
ያ የምጓጓለት ቀን እስከሚመጣ
በንቃት ልጠብቅህ ጸጋህ በኔ ይሁንና
አሜን ኢየሱስ ሆይ እባክህ ቶሎ ና
ነፍሴ ተጠምታሃለች እርካታዋ ነህና
አየዋለው መድሃኔቴ
የአይኔ እረፍት ነህ ኢየሱሴ
አየዋለው መድሃኔቴ
የአይኔ እረፍት ነህ ኢየሱሴ
አየዋለው መድሃኔቴ
የአይኔ እረፍት ነህ ኢየሱሴ
አየዋለው መድሃኔቴ
የአይኔ እረፍት ነህ ኢየሱሴ
ናፍቄአለው እስክትመጣ
እስካገኝህ ከእቅፍህ እስክገባ
አይንህን በአይኔ እስከማየው
በስፍራዬ ሆኜ እፀናለው
አየዋለው መድሃኔቴ
የአይኔ እረፍት ነህ ኢየሱሴ
አየዋለው መድሃኔቴ
የአይኔ እረፍት ነህ ኢየሱሴ
አየዋለው….
አየዋለው መድሃኔቴ
የአይኔ እረፍት ነህ ኢየሱሴ
አለ
በእርግጥ አይሏል ማእበሉ
ቅጥሏል ብሶ ትግሉ
አማራጭ ተስፋ ሲጠፋ
ጊዜውም ሄደ እየከፋ
መጠጊያ ከለላ ቢፈለግ
ሁሉም ሚገባበት ቢያጣ
ከማዶ በባህሩ ላይ
እየተረማመደ መጣ
አይዟቹ አትፍሩ እኔ ነኝ
ያለው የባህሩ ጌታ
ጸጥ አድርጎ ሁሉንም
ማእበሉን ከመንገዴ ገታ
ትናንት ዛረ ዘላለም
ያው ነው አይለወጥ ጌታ
አለ በዙፋኑ ላይ
የኔንም ችግር ሊፈታ *2
አለ አለ የኔ አባት አለ
ትናንትና እንደነበረ ዛረም ደሞ በዚ አለ
ለነገም ተስፋየ እሱ ነው
ዝም ብዬ አመልከዋለው
ተስፋ ሲጨልም ቀኑ ሲመሽ
የተደገፉትም ሲሸሽ
ብቸኝነቱም ሲበረታ
መኖርም ትርጉም ያጣ ለታ
ሸክም ከብዶ ሲያንገላታ
ድካሙ እጅግ ቢበረታ
ወደ እኔ ያለው እየሱስ
እረፍት የሚሰጥ ያለአፍታ
እኔ ካንተጋ ነኝና
አትፍራ ብሎኛል ጌታ
ሸክሜን ያራገፈው
ቀንበሬን ከላዬ እየመታ
ተስፋዬን አድሶ ያቆመኝ
እሱ ነው የነፍሴ ቤዛ
ታሪኬን የቀየረው
እንድኖር በሱ ታዛ
ህይወቴን የቀየረው
እንድኖር በሱ ታዛ
አለ አለ የኔ አባት አለ
ትናንትና እንደነበረ ዛረም ደሞ በዚ አለ
ለነገም ተስፋየ እሱ ነው
ዝም ብዬ አመልከዋለው
አለ በዙፋኑ ላይ የተጨነቀ የሚያይ
አለ ማደሪያው አርጎኛል ውዱ መንፈስ ቅዱስ
አለ በዙፋኑ ላይ የተጨነቀን ሚያይ
አለ በክብር ግርማው ላይ በአብቀኝ በሰማይ
አለ ደሞ በእኔ ውስጥ የነገስታቱ ንጉስ
አለ ማደሪያው አርጎኛል ውዱ መንፈስ ቅዱስ
አለ አለ የኔ አባት አለ
ትናንትና እንደነበረ ዛረም ደሞ በዚ አለ
ለነገም ተስፋየ እሱ ነው
ዝም ብዬ አመልከዋለው